እምነታቸው ምንም ይሁን ምን የግለሰቦችን እኩልነት፣ ክብር እና እምነት እናከብራለን፤ ለማንኛውም አይነት አድልዎ፤ ስደት ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን።
የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ትውፊቷ እና ቅርሷ እንዲጠበቅ እንዲሁም እምነቷን ያለምንም ቅጣት፤ መገለል ካለ ፍርሃት የመተግበር ነፃነት እንዲኖር እናበረታታለን።
በአስተዳደር እና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ እኩል ተሳትፎ እንዲሁም ከመንግስት መዋቅር እና እድሎዎች ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችን ማግለል እንዲቆም እንጠይቃለን።
የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና ማህበረሰቡን ለመከፋፈል የሚደረገውን ጥረት እንቃወማለን ፣ እናም በሁሉም አማኞች መካከል አብሮነትን እና አንድነትን እናበረታታለን ።
በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አይነት ስደት፣ ጥቃት እና የዘር ማጥፋት እንዲቆም፣ ለተጎጂዎች ፍትህ እና ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።
የተፈናቀሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና እንዲሰፍሩ እና ፖለቲካዊ ተኮር የስነ ሕዝብ አወቃቀር ለውጦች እንዲቆሙ እንጠይቃለን።