ስለ እኛ

ተልዕኮ

ራዕይ

MoA Tewahedo's History
ወቅታዊ ትኩረት

እኩልነት እና ፍትህ

እምነታቸው ምንም ይሁን ምን የግለሰቦችን እኩልነት፣ ክብር እና እምነት እናከብራለን፤ ለማንኛውም አይነት አድልዎ፤ ስደት ፍትህ እና ተጠያቂነት እንዲኖር እንጠይቃለን።

የሃይማኖት ነፃነት

የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ትውፊቷ እና ቅርሷ እንዲጠበቅ እንዲሁም እምነቷን ያለምንም ቅጣት፤ መገለል ካለ ፍርሃት የመተግበር ነፃነት እንዲኖር እናበረታታለን።

የሁሉም ተሳትፎ (ሁሉንም የሚያካትት) አስተዳደር

በአስተዳደር እና ውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ላይ እኩል ተሳትፎ እንዲሁም ከመንግስት መዋቅር እና እድሎዎች ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖችን ማግለል እንዲቆም እንጠይቃለን።

አብሮነት እና አንድነት

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እና ማህበረሰቡን ለመከፋፈል የሚደረገውን ጥረት እንቃወማለን ፣ እናም በሁሉም አማኞች መካከል አብሮነትን እና አንድነትን እናበረታታለን ።

ተጠያቂነት

  • ለቀደመው እና አሁን ለተፈፀመው ግፍ ወንጀለኞች በህግ እንዲጠየቁ እና ለተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።
  • ለሟች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈላቸው፣ የተቃጠሉ እና የፈረሱ ቤተክርስቲያናት እና ንብረቶች እንዲገነቡ እና እንዲታደሱ እንጠይቃለን።
  • በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በአማኞቿ ላይ ለደረሰው ጉዳት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ እና እውቅና እንዲሰጠው እንጠይቃለን።

ጥቃትን መከላከል

በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ የሚደርሰው ማንኛውም አይነት ስደት፣ ጥቃት እና የዘር ማጥፋት እንዲቆም፣ ለተጎጂዎች ፍትህ እና ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን።

መመለስና መልሶ ማቋቋም

የተፈናቀሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና እንዲሰፍሩ እና ፖለቲካዊ ተኮር የስነ ሕዝብ አወቃቀር ለውጦች እንዲቆሙ እንጠይቃለን።

የቦርድ አመራር

© 2024, ሞዓ ተዋሕዶ. All Rights Reserved! |
The ሞዓ ተዋሕዶ is not responsible for the content of external sites. Read about our approach to external linking.